የዝቅተኛ-ገቢ የታሪፍ ሙከራ (Low-Income Fare Trial (LIFT))
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
ይህ ገጽ ለመጨረሻ ጊዜ የዘመነው 10/30/2023 ነበር
English 中文 Español Français 한국어 Tiếng Việt
ክፍሎች
አጠቃላይ እይታ
የስጦታ ካርዶች
የትራንዚት ቅናሽ
የውሂብ ጥበቃ
ሌላ
አጠቃላይ እይታ
የዝቅተኛ-ገቢ የታሪፍ ሙከራ (Low-Income Fare Trial (LIFT)) ምንድን ነው?
- የዝቅተኛ-ገቢ የታሪፍ ሙከራ (ሎው-ኢንካም ፌር ትራያል (LIFT)) በሜትሮ እና አውቶቢስ ላይ ቅናሾችን የሚያቀርብ የሙከራ ፕሮግራም ነው። በሎተሪ አማካኝነት፣ ብቁ የሆኑ ኗሪዎች የግማሽ-ዋጋ ቅናሾችን ወይም ነጻ ያልተገደቡ የመስክ ጉዞዎችን ለዘጠኝ ወራት ለማግኘት እድል ያገኛሉ።
LIFT እንደ Metro for DC ተመሳሳይ ፕሮግራም ነው?
- አይ። በዲሴምበር 2022 ተላልፎ የነበረው። የMetro For DC bill፣ በዲሲ ውስጥ ለሚጀመሩ አውቶቡስ ተሽከርካሪዎች የነጻ- ክፍያን የመሳሰሉ ድንጋጌዎችን አካቷል። የነጻ-ክፍያ አውቶቡሶች ትግበራ በመጠባበቅ ላይ ያለ በጀት ነው።
LIFT እንደ WMATA Metro Lift ተመሳሳይ ፕሮግራም ነው?
- አይ። ዝቅተኛ ገቢ ዋጋ ሙከራ ከጃንዋሪ 2023 – ኦክቶበር 2023 ለዲሲ ነዋሪዎች የመጓጓዣ ቅናሾችን የሚሰጥ ፕሮግራም ነው። በ2022 የዲሲ ነዋሪዎች ለሙከራ መርሃ ግብር አመልክተዋል። የWMATA Metro Lift ፕሮግራም በተለይ SNAP ለሚቀበሉ ቤተሰቦች በጁን 2023 የተጀመረው ቀጣይነት ያለው ፕሮግራም ነው።
በዲሲ ውስጥ ሌሎች ምን አይነት የመጓጓዣ ፕሮግራሞች አሉ?
- በSNAP (የቀድሞው ፉድ ስታምፕ) ውስጥ ለሚሳተፉ ቤተሰቦች፦ WMATA በMetro እና አውቶቡስ ላይ “Metro Lift” የተባለ የ50% ቅናሽ ይሰጣል። በመስመር ላይ ወይም በአካል ከWMATA ሶስት ቋሚ የMetro LIFT መመዝገቢያ ቦታዎች መካከል በአንዱ መመዝገብ ይችላሉ። WMATA Metro Liftን በሚመለከት ያለዎትን ጥያቄች WMATAን ለመጠየቅ ወደ 1-888-SmarTrip (888-762-7874) መደወል ይችላሉ።
- 65+ አመትዎ ከሆነ፣ ለ አረጋውያን የ SmarTrip ካርድ ብቁ ነዎት። በአረጋውያን የ SmarTrip ካርድ፣ በምድር ባቡር እና በአውቶቢስ ላይ የግማሽ ዋጋ ቅናሽ ሊያገኙ ይችላሉ። የተወለዱበትን ቀን የሚያሳይ ህጋዊ የመታወቅያ ምስል ሊያስፈልግዎ ይችላል። የአረጋውያን የ SmarTrip ካርድዎን ለማግኘት ወደ የምድር ባቡር ሽያጭ ቦታ ወይም ማንኛውም የማንገመሪ ሃገር መዝገብ ቤት ያምጡት።
[ወደ ላይኛው መመለስ]
የስጦታ ካርዶች
የLIFT ተሳታፊዎች የLIFT ዳሰሳ ጥናትን ስለወሰዱ የ$30 ዲጂታል የስጦታ ካርዳቸውን የሚቀበሉት መቼ ነው?
- በ9/29/2023፣ የዳሰሳ ጥናቱን ለወሰዱ እና መረጃቸው ለLIFT ተሳታፊ በፋይል ላይ ካለን መረጃ ጋር ለሚመሳሰል ሰው ሁሉ ዲጂታል የስጦታ ካርዶችን በኢሜይል ልከናል።
ከLIFT ስለ $25 የስጦታ ካርድ ኢሜይል ወይም የጽሁፍ መልዕክት ደርሶኛል። መልዕክቱ እውነተኛ ነው?
- የስጦታ ካርዶችን ለ LIFT ተሳታፊዎች በኢሜይል እና በጽሁፍ በ7/10/2023, 7/31/2023 እና 8/10/2023 ልከናል። ተጨማሪ ማረጋገጫ ከፈለጉ ለ lift@dc.gov ኢሜይል መላክ ወይም በ202-304-1975 መደወል ይችላሉ።
በዲጂታል የስጦታ ካርድ ፈንታ አካላዊ የስጦታ ካርድ መጠየቅ እችላለሁ?
- አይ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ለአካላዊ የስጦታ ካርድ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ማሟላት አንችልም።
በስጦታ ካርዴ ላይ ችግር ቢያጋጥመኝስ?
- በስጦታ ካርድ ላይ ችግር ካጋጠመዎት (ለምሳሌ የስጦታ ካርዱ ካልሰራ ወይም ከተጠበቀው ያነሰ ዋጋ ካለው)፣ እባክዎ Perfect Gift (ፍጹም ስጦታ)ን በቀጥታ ያግኙ። ለመዝገቦቻችን እንደዚህ ያሉ ችግሮችን ለlift@dc.gov ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፣ ነገር ግን የኛ ሻጭ ብቻ የስጦታ ካርዶቹን ችግሮች መፍታት ይችላሉ፣ እንዲሁም LIFT ምትክ (አዲስ) የስጦታ ካርዶችን አይሰጥም።
የቪዛ ስጦታ ካርዴ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀስ?
- የስጦታ ካርዶቹ እንደ ገንዘብ ይሰራሉ፤ ያ ማለት ሌላ ሰው የስጦታ ካርድ ቁጥር ካለው ሊጠቀምበት ይችላል እና መልሶ ለማግኘት ምንም መንገድ የለም። የስጦታ ካርድዎን ቁጥር በሚስጥር እንዲይዙ እንመክራለን።
በመደብር ውስጥ በአካል በመገኘት ለሚደረጉ ግዢዎች የዲጂታል የስጦታ ካርዴን መጠቀም እችላለሁ?
- በPerfect Gift መሰረት፣ ምናባዊ ቪዛን ወይም የማስተር ካርድ የስጦታ ካርዶችን በመደብር ውስጥ በአካል በመገኘት ለሚደረጉ ግዢዎች መጠቀም አይቻልም። ዲጂታል የስጦታ ካርዶችን በመስመር ላይ ለመግዛት መጠቀም ይችላሉ።
ገንዘቡን ከዲጂታል የስጦታ ካርዴ ወደ LIFT SmarTrip ካርዴ መጨመር እችላለሁ?
- WMATA እንደሚሰሩ ዋስትና መስጠት ስለማይችል፣ WMATA ለመስመር ላይ SmarTrip ካርድ ዋጋ ለመጨመር የስጦታ ካርዶች መጠቀምን አይመከርም።
[ወደ ላይኛው መመለስ]
የትራንዚት ቅናሾች
በLIFT SmarTrip ካርዴ ላይ ገንዘብ አለኝ። ካርዴ ከኦክቶበር 30 በኋላ መስራት ሲያቆም ያ ገንዘብ እንዳልጠፋብኝ እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?
- ገንዘቦችን ለመጠቀም ወይም ለማስተላለፍ አሁን እቅድ ያውጡ!
- ከኦክቶበር 30 ቀነገደብ በፊት በካርድዎ ላይ የቀረውን ገንዘብ ያውጡ።
- አሁንም በካርድዎ ላይ ገንዘብ ካለዎት፣ ወደ WMATA የደንበኛ አገልግሎት (888-762-7874) ደውለው ቀሪ ሂሳብዎን ወደ ሌላ የSmarTrip ካርድ እንዲያስተላልፉ ይጠይቋቸው።
- ሁለቱንም የLIFT SmarTrip ካርድ እና ሌላ የSmarTrip ካርድ ያዘጋጁ። WMATA ሁለቱንም የካርድ ቁጥሮች ይጠይቃል።
- የ“DC LIFT ተሳታፊ” መሆንዎን ለእነሱ መንገርዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
- የጥሪ ማዕከሉ በስራ ቀናት ከ7:00am-8:00pm ድረስ ክፍት ነው።
- ቀሪ ሂሳብ የማስተላለፍ ሂደቱን ለማስኬድ እስከ 2 ቀናት ድረስ ሊወስድ ይችላል
የLIFT ጥቅማጥቅሞቼ ከ10/30 በኋላ መስራት የሚያቆሙት ለምንድን ነው?
- የLIFT ፕሮግራም የተነደፈው የመጓጓዣ ተደራሽነት መጨመር ጥቅሞችን ለማወቅ እንዲረዳን እንደ አጭር ጊዜ “ሙከራ” ወይም የሙከራ ፕሮግራም ነበር። ከዘጠን ወር የሙከራ ጊዜ የተገኘው መረጃ የወደፊት የመጓጓዣ ፖሊሲን ለማሳወቅ ይረዳል።
እኔ የ $25 የቪዛ ስጦታ ካርድን ለመቀበል ተመርጬ ነበር ግን የትራንዚት ቅናሽ አይደለም። ያ ማለት ምን ማለት ነው?
- ይህ ማለት ለሜትሮባስ፣ ሜትሮሬይል፣ ዲሲ ሴርኩላር፣ እና ሌሎች የክልል የአውቶቢስ አጋሮች በመደበኛ ጊዜ እንደሚከፍሉት መክፈል መቀጠል ይችላሉ። ዋጋዎች ተመሳሳይ ሆነው ይቆያሉ።
- አሁንም ስለተመዘገቡ የ $25 የቪዛ ስጦታ ካርድ ይቀበላሉ። የህዝብ መጓጓዣን የበለጠ ተመጣጣኝ ለማድረግ ሲባል የወደፊት ፕሮግራሞችን ለመቅረጽ መጓጓዣ እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዴት እንደሚጠቀሙ መረጃን እንጠቀማለን። የአማራጭ (የሚከፈልባቸው) ዳሰሳዎችን እንዲሞሉ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
- ትራንዚት እና ሌሎች አገልግሎቶች መጠቀምዎን የሚመለከት መረጃን የህዝብ ትራንዚትን የበለጠ ተመጣጣኝ የሚያደርጉ የወደፊት ፕሮግራሞችን መልክ ለማስያዝ የምንጠቀም ይሆናል። የአማራጭ (የሚከፈልባቸው) ዳሰሳዎችን እንዲሞሉ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
በሎተሪው ውስጥ የግማሽ-ዋጋ ቅናሽ ተቀብያለሁ። ያ ማለት ምን ማለት ነው?
- ይህ ማለት በሜትሮባስ፣ ሜትሮሬይል፣ ዲሲ ሴርኩሌተር፣ እና ሌሎች የክልል የአውቶቢስ አጋሮች ላይ የመደበኛ ዋጋ ግማሽ፣ በዚህ የSmarTrip ካርድ፣ ለዘጠኝ ወራት፣ ይቀነስልዎታል ማለት ነው። ከመጠቀምዎ በፊት ወደ LIFT SmarTrip ካርድዎ ገንዘብ መጨመር ያስፈልግዎታል። ይህን በ ኦላይን፣ በ Metrorail ጣቢያ፣ በ Metrobus ላይ፣ ወይም በተመረጡ የችርቻሮ መደብሮች፣ እንደ CVS እና Giant ማድረግ ይችላሉ።
- ካርድዎን ለመውሰድ የማረጋገጫ ቁጥር እና መመሪያ የያዘ ኢሜይል፣ የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ደብዳቤ እንልክልዎታለን። እርስዎ ወይም የሚያምኑት ሰው የእርስዎን የማረጋገጫ ቁጥር ማምጣት አለባችሁ የLIFT SmarTrip ካርድዎን ከ WMATA በ 655 Virginia Ave SW, Washington, DC 20024 በ መጥታችው ለመውሰድ። የሥራ ሰዓታት ሰኞ 8-4፣ ማክሰኞ 8-2:30፣ እሮብ-ዓርብ 8-4 ናቸው። በዚህ ጊዜ፣ የእርስዎን የLIFT SmarTrip ካርድ መላክ አንችልም።
- ቅናሹ ካርድዎን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠቀሙ ይጀምራል እና በኦክቶበር 30, 2023 ያበቃል።
>
- እንዲሁም ስለተመዘገቡ የ $25 የቪዛ ስጦታ ካርድ ይቀበላሉ።
- ትራንዚት እና ሌሎች አገልግሎቶች መጠቀምዎን የሚመለከት መረጃን የህዝብ ትራንዚትን የበለጠ ተመጣጣኝ የሚያደርጉ የወደፊት ፕሮግራሞችን መልክ ለማስያዝ የምንጠቀም ይሆናል።
- የአማራጭ (የሚከፈልባቸው) ዳሰሳዎችን እንዲሞሉ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
በሎተሪው ውስጥ ነጻ ያልተገደቡ ጉዞዎችን ተቀብያለሁ። ያ ማለት ምን ማለት ነው?
- ይህ ማለት በሜትሮባስ፣ ሜትሮሬይል፣ ዲሲ ሴርኩሌተር፣ እና ሌሎች የክልል የአውቶቢስ አጋሮች ላይ፣ በዚህ የSmarTrip ካርድ፣ ለዘጠኝ ወራት፣ በነጻ ይጓዛሉ ማለት ነው። ይህን የSmarTrip ካርድ የሜትሮ ጣቢያዎች እና አውቶቢሶች ውስጥ ሲገቡ ወዲያውኑ መጠቀም ይችላሉ–በትራንዚት ዋጋ ወይም ሌሎች ማለፊያዎች መጫን አይጠበቅብዎትም። የነጻ ታሪፍ በከፍተኛ ሰዓታት ወቅት እንኳ ተግባራዊ ይሆናል።
- ካርድዎን ለመውሰድ የማረጋገጫ ቁጥር እና መመሪያ የያዘ ኢሜይል፣ የጽሁፍ መልእክት እና/ወይም ደብዳቤ እንልክልዎታለን። እርስዎ ወይም የሚያምኑት ሰው የእርስዎን የማረጋገጫ ቁጥር ማምጣት አለባችሁ የLIFT SmarTrip ካርድዎን ከ WMATA በ 655 Virginia Ave SW, Washington, DC 20024 በ መጥታችው ለመውሰድ። የሥራ ሰዓታት ሰኞ 8-4፣ ማክሰኞ 8-2:30፣ እሮብ-ዓርብ 8-4 ናቸው። በዚህ ጊዜ፣ የእርስዎን የLIFT SmarTrip ካርድ መላክ አንችልም።
- ነፃ ታርፉ ካርድዎን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠቀሙ ይጀምራል እና በኦክቶበር 30, 2023 ያበቃል።
- እንዲሁም ስለተመዘገቡ የ $25 የቪዛ ስጦታ ካርድ ይቀበላሉ።
- >የአማራጭ (የሚከፈልባቸው) ዳሰሳዎችን እንዲሞሉ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
የLIFT ቅናሽ እንደሚወስድ ማን ይወስናል?
- የLIFT ትራንዚት ቅናሾች በመላው ሎተሪ ውስጥ በዘፈቀደ ይሰጣሉ።
- የሎተሪ መመረጥዎን ይግባኝ ለማለት ሂደት የለም።
ይህን የትራንዚት ቅናሽ ምን የተለዩ የአውቶቢስ እና የባቡር አማራጮች ላይ መጠቀም እችላለሁ?
የLIFT SmarTrip ካርድዎን በዲሲ ትራንዚት፣ ሜትሮባስ እና ሜትሮሬይል እና የዲሲ ሴርኩሌተር ላይ በመደበኛነት እንደሚጠቀሙት መጠቀም ይችላሉ። እንዲሁም በሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ውስጥ የተወሰኑ የትራንዚት ሲስተሞች ላይ መጠቀም ይችላሉ፣
- አርሊንግተን ትራንዚት (Arlington Transit (ART))፣
- የፌይርፋክስ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ሃይል-መቆጠቢያ አውቶቢስ ሲስተም (City of Fairfax-University Energysaver Bus System (CUE))፣
- ድራይቪንግ አሌክሳንድሪያ ሴፍሊ ሆም (Driving Alexandria Safely Home (DASH))፣
- የፌይርፋክስ ኮኔከተር (Fairfax Connector)፣
- የፕሪንስ ጆርጅ ካውንት ውስጥ ባስ (TheBus in Prince George’s County)፣
- የራይድኦን አውቶቢሶች በሞንትጎሜሪ ካውንቲ ውስጥ (RideOn buses in Montgomery County)፣
- የላውዱን ካውንቲ ትራንዚት (Loudoun County Transit)፣
- እና ኦምኒራይድ ከፖቶማክ እና ራፓሃኖክ ትራንዚት ኮሚሽን (OmniRide from the Potomac and Rappahannock Transit Commission (PRTC)) ጨምሮ።
LIFT በ MetroAccess ላይ ቅናሽ ያደርጋል?
- አይ፣ LIFT በ MetroAccess ላይ ቅናሽ አያደርግም። LIFT SmarTrip ካርድ የሚቀበሉት Metrorail፣ Metrobus፣ እና የክልል የአውቶቢስ አጋሮች ላይ ቅናሾችን ይሰጣል።
የLIFT SmarTrip ካርዴ ላይ በSmarTrip የሞባይል መተግበሪያ ወይም ኦንላይን አማካኝነት ዋጋ መጨመር እችላለሁ?
- አዎ፣ በSmarTrip መተግበሪያ አማካኝነት ወይም ኦንላይን ካርድዎን ማስመዝገብ፣ ማለፊያዎችን መግዛት፣ እና ካርድዎ ላይ ዋጋን መጨመር ይችላሉ።
- በሎተሪው ውስጥ ነጻ ያልተገደቡ ጉዞዎችን ከተቀበሉ፣ ማለፊያዎችን ወይም ዋጋን መጨመር አያስፈልግም። ሁሉም ጉዞዎችዎ በነጻ ይሆናሉ። አሁንም ከፈለጉ ካርድዎን ኦንላይን ማስመዝገብ ይችላሉ።
የLIFT SmarTrip ካርዴን ወደ ሞባይሌ ማስተላለፍ እችላለሁ (በአፕል ዋሌት ወይም ጉግል ፔይ አማካኝነት)?
አይ፣ የእርስዎ የLIFT SmarTrip ካርድዎ በአፕል ዋሌት ወይም ጉግል ፔይ አማካኝነት ወደ ስልክዎ ላይ መጨመር አይችልም። ይህ ማለት ስልክዎን በመጠቀም ሜትሮ ወይም አውቶቢስ ላይ መግባት አይችሉም–ካርድዎን መጠቀም ይኖርብዎታል።
የLIFT SmarTrip ካርዴን መሸጥ እችላለሁ?
አይ፣ እባክዎ የLIFT SmarTrip ካርድዎን አይሽጡ። ይህ ካርድ እንዲጓዙ ለመርዳት የታሰበ ነው።
የLIFT SmarTrip ካርዴን ማጋራት እችላለሁ?
የLIFT SmarTrip ካርድዎን ለራስዎ የሜትሮ እና አውቶቢስ ጉዞዎች እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን፣ ግን ማጋራት ቅጣት የለውም።
ነጻ ያልተገደቡ ጉዞዎችን ወይም የግማሽ-ዋጋ ቅናሽን ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም እችላለሁ?
ቅናሽዎ በኦክቶበር 30, 2023 ያበቃል። ከአገልግሎት ማብቂያ ቀን በኋላ፣ የLIFT SmarTrip ካርድዎ አይሰራም። ለሜትሮ እና ለአውቶቢስ መክፈልን በመደበኛው ጊዜ መልሰው መጀመር ይችላሉ።
የእኔ የLIFT SmarTrip ካርድ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀስ?
- የLIFT SmarTrip ካርድዎ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ፣ እባክዎ በ lift@dc.gov ያግኙን ወይም DOEE'ን በ 202-304-1975 ያነጋግሩ። የጠፋውን ወይም የተሰረቀውን ካርድ እንዳይሰራ እናደርጋለን እና አዲስ በፖስታ እንልክልዎታለን።
በLIFT ወቅት በሌሎች የዲሲ መንግስት ፕሮግራሞች ውስጥ እንዲሳተፍ ይፈቀድልኛል?
- የLIFT ውስጥ ተሳትፎዎ ከDOEE ወይም ሌሎች የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች በመደበኛነት የሚያገኙት ጥቅማጥቅሞች እና አገልግሎቶች ላይ ተጽዕኖ የለውም፣ ግን እርስዎ ሜትሮ ወይም አውቶቢስ ላይ በግል ደረጃ የአረጋውያን፣ አካል ጉዳተኛ፣ ወይም የተማሪ ቅናሽ የሚወስዱ ከሆነ ለLIFT ብቁ አይሆኑም። ይህ የሚጨምው ነጻ ወይም የቅናሽ ታሪፍ ፕሮግራም ለአረጋውያን እና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች ወይም ኪድስ ራይድ ፍሪ እና የጎልማሳ ተማሪ ትራንዚት ድጎማ ለተማሪዎች ነው።
[ወደ ላይኛው መመለስ]
የውሂብ ጥበቃ
የዲሲ መንግስት መረጃዬን እንዴት ይጠቀማል?
ለኗሪዎች የትራንዚት ቅናሾችን ከማቅረብ በተጨማሪ፣ ይህ ፕሮግራም እኛን–የዲሲ መንግስት–እነዚህ የትራንዚት ቅናሾች ኗሪዎች እንዴት እንደሚጓዙ፣ እንዲሁም፣ ስራቸው፣ ገቢያቸው፣ ቤተሰባቸው፣ ጤናቸው፣ እና የሃይል አጠቃቀማቸው ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያመጡ ለማወቅ ይረዳናል። የእርስዎን ማንነት እና ብቁነት ለማረጋገጥ መረጃዎን እንጠቀማለን። ደግሞም መረጃዎን ለሚከተለው ልንጠቀም እንችላለን፦
- SmarTrip ካርድ እና/ወይም የስጦታ ካርድ ለእርስዎ ለመላክ፣
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣
- ጥያቄዎችዎን ለመመለስ፣
- አማራጭ፣ የተከፈሉ የዳሰሳ ጥናቶች ለእርስዎ ለመላክ፣ እና
- ይህ ፕሮግራም እርስዎ እና የሌላ ዲስትሪክት ነዋሪዎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደረ ለመገምገም
የእኔ ውሂብ እንዴት ይጠበቃል?
- እኛ–የDC መንግስት– ውሂብዎን እንደ ሚስጥራዊ እና የተጠበቀ መረጃ እንይዘዋለን፣ ማለትም ውሂብዎን በአስተማማኝ ሁኔታ እናስቀምጣለን እና ውሂብዎን በተመሰጠሩ ኮምፒተሮች ላይ እናክላለን። ውሂብዎን በፍጹም ኢሜይል አናደርግም፣ ኦንላይን ላይ አንለጥፈውም፣ ወይም ባልተመሰጠሩ ሰርጦች እንዲገኝ አናደርገውም።
- ውሂብዎን LIFT እንዴት እየሰራ እንደሆነ ለመረዳት ብቻ እንጠቀመዋለን። ውሂብዎን በህግ ካልተፈለገ በስተቀር፣ ከአስተዋዋቂዎች ወይም ከህግ አስከባሪዎች ጋር አንጋራም።
- በምናሳትማቸው ማንኛውም የምርምር ግኝቶች የእርስዎ ወይም የሌላ ማንኛውም ተሳታፊዎች ስሞችን ወይም የግል መረጃዎችን አያካትትም።
- ጥናቱ እንደተጠናቀቀ፣ የግል መረጃዎን ማግኘት ወይም መጠቀም አንችልም። የምንናገረው ማንኛውም ውሂብ የእርስዎ ወይም የሌላ ማንኛውም ተሳታፊዎች ስሞችን ወይም የግል መረጃዎችን አያካትትም። በተቻለ መጠን፣ ሙሉ በሙሉ ውሂብዎን እናስወግዳለን።
በዚህ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፍ ከሆነ ወደፊት ያነጋግሩኛል?
አዎ። ስለ ትራንዚት አጠቃቀምዎ እና በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉዎትን ተሞክሮ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ የዚህ ፕሮግራም መላው ዘጠኝ ወር ውስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ልናናግርዎት እንችላለን።
የእኔን የማህበራዊ ዋስትና ወይም የA-ቁጥር እንዲሰጥ ለምን እጠየቃለሁ?
- የእርስዎን የማህበራዊ ዋስትና ወይም የA-ቁጥር ማንነትዎን ለመለየት እና ለLIFT ያለዎትን ብቁነት ለማረጋገጥ እንጠቀማለን። እንዲሁም LIFT የተሳታፊዎችን ገቢ፣ ጤና፣ ሥራ እና ሌሎች የደኅንነት ውጤቶችን እያሻሻለ መሆኑን ለማየት ያንን መረጃ እንጠቀማለን።.
ስለ የእኔ ዘር እና ጎሳ መረጃ እንድሰጥ ለምን እጠየቃለሁ?
- LIFT የዲሲ መንግስት ነዋሪዎች እንዴት እንደሚመላለሱት ላይ እንዲሁም በስራቸው፣ በገቢያቸው፣ በቤተሰባቸው፣ በጤና እና በሃይል አጠቃቀማቸው ላይ የመጓጓዣ ቅናሾች እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ላይ የዘር ልዩነቶች ይኖሩ እንደሆነ ለማወቅ እንዲረዳ ስለ ዘርዎ መረጃዎን ይሰበስባል።
[ወደ ላይኛው መመለስ]
ሌላ
ለLIFT የእውቂያ መረጃዬን እንዴት ማዘመን እችላለሁ?
- በLIFT ከተመዘገቡ ወዲህ አድራሻዎ፣ ስልክ ቁጥርዎ ወይም ኢሜልዎ ከተቀየረ፣ እባክዎን ለእኛ ለመንገር ይህንን ቅጽ ይጠቀሙ።
ስለ DOEE የፍጆታ አቅም ፕሮግራሞች ወይም የፍጆታ ሂሳቦቼ ጥያቄዎች አሉኝ። ልትረዱኝ ትችላላችሁ?
- እባክዎ በ202-535-2600 በመደወል ወይም doee@dc.gov ኢሜይል በመላክ እነዚያን ጥያቄዎች ለዲሲ የሃይል እና የአካባቢ ጥበቃ መምሪያ (DOEE) ያስተላልፉ።
ስለ WMATA Metro Lift ጥያቄዎች አሉኝ። ልትረዱኝ ትችላላችሁ?
- WMATA የWMATA Metro Liftን ያስተዳድራል፣ ስለዚህ ሰራተኞቻቸው ጥያቄዎችዎን ለመመለስ የበለጠ ምቹ ናቸው። WMATA Metro Liftን በሚመለከት ያለዎትን ጥያቄች WMATAን ለመጠየቅ ወደ 1-888-SmarTrip (888-762-7874) መደወል ይችላሉ።
[ወደ ላይኛው መመለስ]
ስለ LIFT እዚህ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ በ lift@dc.gov ያግኙን ወይም LIFT'ን በ 202-304-1975 ያነጋግሩ። በአማርኛ፣ ማንዳሪን ወይም ስፓኒሽ ሊያናግሩን ከፈለጉ፣ ለእርስዎ እና ለአስተርጓሚ ልንደውል እንችላለን። አገልግሎቱ ነጻ ነው።